Гуру Песен Популярное
А Б В Г Д Е Ж З И К Л М Н О П Р С Т У Ф Х Ц Ч Ш Э Ю Я
# A B C D E F G H I J K L M N O P Q R S T U V W X Y Z

BEZUAYEHU DEMISSIE / Ethiopia - መለየት ክፉ እጣ Meleyet Kifu Eta Lyrics (http://vk.com/beauty_of_africa) | Текст песни

ተስለሻል እንዴ ካይኔ ከመሃሉ
አንቺ ብቻ እኮ ነሽ በሚታየኝ ሁሉ
ተስለሻል እንዴ ካይኔ ከመሃሉ
አንቺ ብቻ እኮ ነሽ በሚታየኝ ሁሉ
አንቺ ብቻ እኮ ነሽ በሚታየኝ ሁሉ

የዳመናውን ጭስ ወደላይ አይኔ ተከትሎ
የዳመናውን ጭስ ወደላይ አይኔ ተከትሎ
ባሳቡያይሻል ከማዶ ላይ ስሎ: ከማዶ ላይ ስሎ
የሚጣፍጥ ህመም ስሜት ነው ቅር የሚል ደስታ
የሚጣፍጥ ህመም ስሜት ነው ቅር የሚል ደስታ
ሙሉው ጎዶሎ ነው ትርጉሙ ትዝታ: ትርጉሙ ትዝታ
ከኔ አንጀት ይመስል ይገርማል የተሰራው ክሩ
ከኔ አንጀት ይመስል ይገርማል የተሰራው ክሩ
ይረበሻል ሆዴ ሲገረፍ ክራሩ: ሲገረፍ ክራሩ

አይታይሽም ወይ የኔ አበባ የልቤ ውስጥ እሳት
ስንቱን አሳለፍኩት የኔ አለም አንቺን ላለመርሳት
ሳድር ለብቻዬ የኔ አበባ ስወድቅ ስነሳ
አስታውስሻለሁ የኔ አለም እኔ አንቺን አልረሳም

ሰማይ ደም ቢመስልም ብትጠቁር ጨረቃ
ሳላይሽ አላድርም እኔ አልችልም በቃ: አልችልም በቃ
ደመናው ተቀዶ ዶፍ ቢወርድ ከሰማይ
አልችልም ለማደር አይኖችሽን ሳላይ: አንቺን ሳላይ

ምን ጉድ ነው መለየት ክፋቱ
ጨክኗል ተመዟል ካፎቱ
ሊለየን ሊያርቀን ቢነሳም
አይችልም እኔ አንቺን አልረሳም
ምን ጉድ ነው መለየት ክፋቱ
ጨክኗል ተመዟል ካፎቱ
ሊለየን ሊያርቀን ቢነሳም
አይችልም እኔ አንቺን አልረሳም

ተስለሻል እንዴ ካይኔ ከመሃሉ
አንቺ ብቻ እኮ ነሽ በሚታየኝ ሁሉ
ተስለሻል እንዴ ካይኔ ከመሃሉ
አንቺ ብቻ እኮ ነሽ በሚታየኝ ሁሉ
አንቺ ብቻ እኮ ነሽ በሚታየኝ ሁሉ

ስንቱን ጋራ ዙረሽ የኔ አለም ስንቱን ጋራ ዞሬ
ስንቱን ጋራ ዙረሽ የኔ አለም ስንቱን ጋራ ዞሬ
እንዴት እንዳዲስ ሰው ታሚኛለሽ ዛሬ:ታሚኛለሽ ዛሬ
እስኪ ልጠይቀው ጥርስሽን ምን ይሆን ምክንያቱ
እስኪ ልጠይቀው ጥርስሽን ምን ይሆን ምክንያቱ
ፈገግ ብሎ ሸኘኝ ሲቆረጥ አንጀቱ: ሲቆረጥ አንጀቱ
ከኔ አንጀት ይመስል ይገርማል የተሰራው ክሩ
ከኔ አንጀት ይመስል ይገርማል የተሰራው ክሩ
ይረበሻል ሁዴ ሲገረፍ ክራሩ: ሲገረፍ ክራሩ

አይታይሽም ወይ የኔ አበባ የልቤ ውስጥ እሳት
ስንቱን ኣሳለፍኩት የኔ አለም አንቺን ላለመርሳት
ሳድር ለብቻዬ የኔ አበባ ስወድቅ ስነሳ
አስታውስሻለሁ የኔ አለም እኔ አንቺን አልረሳም

ሰማይ ደም ቢመስል ብትጠቁርም ጨረቃ
ሳላይሽ አላድርም እኔ አልችልም በቃ: አልችልም በቃ
ደመናው ተቀዶ ዶፍ ቢወርድ ከሰማይ
አልችልም ለማደር አይኖችሽን ሳላይ:አንቺን ሳላይ

ምን ጉድ ነው መለየት ክፋቱ
ጨክኗል ተመዟል ካፎቱ
ሊለየን ሊያርቀን ቢነሳም
አይችልም እኔ አንቺን አልረሳም
ምን ጉድ ነው መለየት ክፋቱ
ጨክኗል ተመዟል ካፎቱ
ሊለየን ሊያርቀን ቢነሳም
አይችልም እኔ አንቺን አልረሳም
ምን ጉድ ነው መለየት ክፋቱ
ጨክኗል ተመዟል ካፎቱ
ሊለየን ሊያርቀን ቢነሳም
አይችልም እኔ አንቺን አልረሳም

BEZUAYEHU DEMISSIE / Ethiopia еще тексты


Статистика страницы на pesni.guru ▼
Просмотров сегодня: 1
Видео
Нет видео
-